Graduation
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ በ 14 ቱም ኮሌጆች ከደረጃ 1 አስከ 5 በቀንና በማታ ያሰለጠናቸዉን 6244 ሰልጣኞችን በሚሊኒዬም አዳራሽ አስመርቀዋል፡፡
በምርቃ ስነ ስርዓት ላይ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትና የእለቱን የክብር እንግዶችን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ እንደተናገሩት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ዉጤት ተኮር የስልጠና ስነ ዜዴ በመከተል ብቁና ተወዳዳሪ የሰዉ ሃይል በማፍራት ለእንዱስትሪ ገበያ እንደሚያቀርብና ለኢንቴርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ድጋፍ በመስጠት ምርትማነታቸዉን እንዲያሻሽሉ ለማድረግ እየሰራ የሚገኝ ዘርፍ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ኃፊዋ አክለዉም ዘርፋ የሚፈለገዉን የሰዉ ሃይል በብቃትና በጥራት ለማዉጣት 14 ቱም ኮሌጆች ባደረጉት ጥረት የብቃት ምዘና ተፈትነዉ ያለፉና ለዛሬ ምረቃ የበቁትን ሰልጣኞችን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ልባዊ ምኞታቸዉን ገልጸዉ ዘርፉ በከተማ አስተዳደሩ ትኩረት በማግኘቱ ገበያ የሚፈልገዉን የሰለጠነ፤ ብቃትና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት በአሰራር፤ በአደረጃጀትና በግብዓት ለማሻሻል የርፎርም ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
በእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ከንተባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡





