ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች የመጡ የ GIZ country ዳይሬክተሮች በአዲስአበባ  ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አደርጉ ። GIZ country directors from different African countries exchanged experience and visited Addis Ababa Tegbare-id Polytechnic College.







ተግባረእድ ሚዲያ

የኮሌጃችን ዋና ዲን አቶ ግሩም ግርማ አዲስ አበባ ተግባረእድ  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ መሠርት በማድርግ  በዉጤት የሚገለፁ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ ነው ብለዋል ።

የISO 9001:2015  የጥራት አመራር ስርዓት ለመተግበረ  ከታህሳስ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተግባር በመግባት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቶ ኮሌጁን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ብሎም ከከተማ አስተዳደር እሴት እዉቅና ማግኘቱን ገልፀዋል ።

GIZ ከሚተገበርባቸው  ፕሮጀክቶች የኢትዩጵያ እና የጀርመን ገቨርመንት የትብብር  ማዕቀፍ ውስጥ በGIZ በኩል KFW፣ STEEP ፣ sport for development  አጠቃላይ ቲቬት  ተቋማት የተሰሩ ስራዎች ተግባረእድ  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  እንደ ማሳያነት የተመረጠ ሲሆን  ለወደፊትም አብርው እንደሚሰሩ ገልፀዋል ።

በመጨርሻም  በኢንኩቤሽን ሴንተር ፣ በአውቶሞቲቭ ፣ ጋርመንትና ቴክስታይል የስልጠና ዘርፎች ጉብኝት አድርገዋል።

ተግባረእድ ኮሚዩኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *